አንዳንድ ሰዎች የወንጌል ስብከት ተግባርን ለሰባኪዎች፣ ለአቅበተ እምነት አስተማሪዎች፣ ወይም ለመጽሐፍ ቅዱስ መምህራን ብቻ ትተውታል። ነገር ግን አዲሱ ኪዳን ሁሉም ክርስቲያን አገልጋይ እንደ ሆነ እና ወንጌልን ሊሰብክ እንደሚገባ ይናገራል።
• ምሳሌ ትተውልናል፦ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች በኑሯቸው ሁሉ ወንጌልን ይሰብኩ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፦ “የተበተኑትም በሄዱበት ሁሉ ቃሉን ሰበኩ” (የሐዋርያት ሥራ 8፥4፤ 11፥19-21)። ሁሉም ደቀ መዛሙርት ከኢየሩሳሌም በተበታተኑ ጊዜም ወንጌሉን እየተናገሩ እንደ ነበር እናነብባለን።
• ታዝዘናል፦ ጴጥሮስ በመልእክቱ፣ “በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያት ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን በፍርሀት እና በየዋህነት ይሁን” ይለናል(1ኛ ጴጥሮስ 3፥15)።
• ፍቅር ግድ ይለናል፦ ጎረቤታችንን እንደ ራሳችን መውደድ ካለብን (ማርቆስ 12፥31፤ ያዕቆብ 2፥8)፣ ወንጌልን ለእርሱ/ሷ ከመናገር በላይ እውነተኛ መውደድ ከየት ይገኛል?