“ገላጭ” ስብከት ምንድን ነው?

መልስ

ገላጭ ስብከት የምንሰብከውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ማዕከላዊ ሐሳብ የስብከቱ አንኳር ሐሳብ በማድረግ፣ አሁን ላለ ነባራዊ ሁኔታ የሕይወት ተዛምዶ የሚሠራበት የስብከት ዐይነት ነው።

በሌላ አነጋገር፣ ገላጭ ስብከት የአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍልን ትርጉም ነቅሶ አውጥቶ፣ ለሰሚዎቹ አሁን ላሉበት ሕይወት ጠቃሚ በሆነና ትርጉም ባለው መንገድ ያሳያል። አጠር ባለ አነጋገር የገላጭ ስብከት ትርጉም ይኽው ነው።

ስለ ገላጭ ስብከት ይህን ካልን ገላጭ ስብከት ምን እንዳልሆነ ደግሞ እንመልከት፦

  1. ገላጭ ስብከት ግዴታ አንድ ወይም ሁለት ቁጥሮች ላይ ማተኮር የለበትም፤
  2. ገላጭ ስብከት ግዴታ የተወሳሰቡ የትርጉም ትንታኔዎች ወይም ረጃጅም ታሪካዊ ዳራ ማቅረብ አይገባውም፤
  3. ገላጭ ስብከት ደረቅ፣ ሕይወት አልባና ከሰዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ የተፋታ መሆን የለበትም፤
  4. የክፍሉን ዋና ሐሳብ ለፈለገው የሕይወት ተዛምዶ በመጠቀም፣ የክፍሉ ሐሳብ ግልጽ እንዳይሆን ግርታን መፍጠር የለበትም (ይህ ማለት አንድን የመጽሐፍ ክፍልን ጠምዝዘን የፈለግነውን ነገር ማስባል ማለት ነው)።

በተቃራኒ ትንሽ ትልቅም ሆነ መካከለኛ ቁጥሮች ያሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ቢሆን፣ ዓላማው ተውኔታዊ በሆነ መንገድ የክፍሉን ዋና ሐሳብ አሁን ላለንበት ዓለም ጠቃሚ በሆነ መንገድ ማቅረብ ነው።