ወንጌል ስብከትን በተመለከተ ያሉ መጥፎ ልማዶች

1. ወንጌሉን ከነጭራሹ አለመናገር፦ ወንጌል መስበክ ማለት የምሥራቹን ቃል መናገር ማለት ነው፤ ስለዚህ ትልቁ ጥፋት የሚሆነው ከነጭራሹ አለመናገር ነው። አንዳንድ ግዜ ማኅበራዊ ሥራ የሚሠሩ ክርስቲያኖች፣ ሰዎችን በመርዳትና በመንከባከብ ወንጌል የሰበኩ ይመስላቸዋል። ነገር ግን ስለ ክርስቶስ ሳንናገር ወንጌል ስብከት የለም።

2. ወንጌሉን አጉድሎ መናገር፦ ታማኝነት ያለው ወንጌል መሥራት ማለት መልእክቱን በሙሉ መናገር ማለት ነው (ሐዋርያት 20፥27)። ብዙ ስለማይነገርለት የኀጢአት እውነት እና ስለ እግዚአብሔር ፍርድ ጭምር መናገር አለብን።

3. በወንጌሉ ፈንታ የተሳሳተ ትምህርት ማስተማር፦ አንዳንድ ሰዎች ወንጌሉን ፊት ለፊት የሚቃወም ትምህርት እያስተማሩ፣ ወንጌል እያስተማርን ነው በማለት ሰሚዎቻቸውን ያስታሉ (ገላትያ 1፥6-92ኛ ጴጥሮስ 2፥1-3)።

4. ወንጌሉን እንደ አማራጭ ማቅረብ፦ ማመን ግዴታ ያልሆነበት እና ምንም አደጋ እንደማያስከትል የግል አመለካከት አድርጎ ወንጌሉን እንደ አማራጭ መናገር በራሱ ትልቅ ስሕተት ነው። ወንጌል መስበክ ማለት ሰዎች ከእግዚአብሔር ዘላለማዊ ቁጣ እንዲያመልጡ፣ በክርስቶስ እንዲያምኑ እና ንስሓ እንዲገቡ መናገር ነው። ወንጌል ግላዊ አመለካከት አይደለም፤ ስንሰብክም የወንጌሉን አጠቃላይ እውነት እና ሌሎች መገለጫዎቹን መናገር ይኖርብናል።

5. ውሳኔ እንዲያደርጉ ማስገደድ፦ እምነት እና መመለስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። ሰዎች እኛ አስገድደናቸው ቢያምኑ እንኳ፣ ውሳኔያቸው ለዘላለሙ ሕይወት ምንም ጥቅም የሌለው ነው። እንዲህ ማድረግ አንድ ሰው ንስሓ ሳይገባ እና በክርስቶስ ሳያምን ክርስቲያን ነኝ ብሎ እንዲያስብ ያደርገዋል።

6. ለድነት የማይጠቅሙ ሐሳቦችን ማግነን ያላመኑ ሰዎችን ጥያቄ መመለስ ቢኖርብንም፣ ስለ ክፉት መኖር ፍልስፍና እያወሩ ሰዓታትን ማሳልፍ፣ ስለ ክርስቶስ ከማውራት ጋር አንድ አይደለም። ትናንሽ ነገሮች ስለ መስቀሉ ከማውራት ሊገድቡን አይገባም።

7. ያላመኑ ሰዎችን ጥያቄ አግባብነት በሌለው መልኩ መመለስ፦ ይህ እነርሱን የሚያስቆጣ እና በቀጣይም ወንጌሉን እንዳንናገር የሚከለክል ነው። ጴጥሮስ ስለዚህ ነገር በመልእክቱ አስጠንቅቆናል፤ “እናንተ ስላላችሁ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በትሕትናና በአክብሮት አድርጉት”(1ኛ ጴጥሮስ 3፥15-16)።